Categories: Uncategorized

ሜዳ ኮድን እንዴት አሳደግነው?

ኪው.አር ኮድ QR CODE እ.ኤ.አ በ1994 ዓ.ም በጃፓን የተፈጠረ የሁለት ልኬት (two dimensional) የሆነ የባር ኮድ (Barcode) አይነት ነው። ባርኮድ ለረጅም ዓመታት ውሂብ (data) በሚታይ መልኩ በመግለጥ በተለይ ለዕቃዎች ልዩ መለያ በመሆን በመጋዘኖች፣ በሱቆችና መደብሮች፣ በመጓጓዣ ቦታዎች አገልግሎት ላይ ይውል ነበር። አሁንም እየዋለ ነው።

በሀገራችን ባለው ዝቅተኛ የቴክኖሎጂ ቅቡልነት ኪውአር ኮድ እምብዛም የተለመደ ባይሆንም በተቀረው ዓለም ግን ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች ላይ ይውላል። ልክ እንደ ባርኮድ ለዕቃዎች ልዩ መለያ መሆንን ጨምሮ የቢዝነስ ካርድ፣ ማስፈንጠሪያ (link)፣ የመክፈያ አማራጭ፣ የዝግጅቶች እና ሁነቶች መግቢያ ቲኬት፣ የአቴንዳንስ መመዝገቢያ፣ ፋይል መላላኪያ እንዲሁም ብዙ ኑሮን የሚያቀሉ አገልግሎቶች ላይ በመግባት ጥቅም ላይ ይውላል።

ሜዳ ለኢትዮጵያዊያን ኪውአር ኮድን ጨምሮ ኑሮን የሚያቀሉ የተለያዩ አማራጮችን ሰብስቦ የያዘ ነው። በእኛ እምነት ሰዎች የየዕለት ኑሯቸው ላይ የዲጂታል አማራጮች በበዙ እና በሰፉ ቁጥር ኑሮ ይቀላል። ለምሳሌም አንድ የሜዳ ተጠቃሚ ቀኑን ሲጀምር ዜና ማየት፣ ከወዳጆቹ ጋር መልእክት መላላክ የቀኑን የአየር ሁኔታ መመልከት እና የመሳሰሉትን ሜዳ ላይ ማከናወን ይችላል። እንዲሁም ቀኑን ከጀመረ በኋላ የትራንስፖርት አገልግሎቶች መጠቀም፣ ክፍያዎችን በቀላሉ መፈፀም፣ የአየር ሰዓት መግዛት፣ የተለያዩ ዝግጅቶች መግቢያ ቲኬቶችን መቁረጥ እና የመሳሰሉትን አሁንም ከሜዳ ሳይወጣ መፈፀም ይችላል።

እነዚህን ሁሉ አገልግሎቶች በአንድ ቦታ በዲጂታል ማግኘት መቻል አንድ ትልቅ ነገር ቢሆንም፣ ደረሰኝ መቀበል እና አገልግሎቶቹን ለማግኘት ረጃጅም ቅጽ (ፎርም) መሙላት ሊያስፈልግ ግድ የሚልባቸው  አገልግሎቶችም አሉ። ታዲያ ይህን ችግር ለመፍታት ኪውአር ኮድን መጠቀም ነገሩን ቀላል ያደርገዋል። ሜዳ ላይ የምንጠቀመውን ኪው.አር ኮድ ሜዳ ኮድ በማለት ለተለያዩ አገልግሎቶች አውለነዋል። ይህን በማድረጋችን ተጠቃሚዎች ሜዳ ላይ የሚኖራቸው ቆይታ ቀላል እና የተመቸ እንዲሆን አድርጎልናል።

የተጠቃሚ መታወቂያ

የመጀመሪያውና ዋናው የሜዳ ኮድ የተጠቃሚ መታወቂያ ነው። አንድ የሜዳ ተጠቃሚ በሚፈጠርለት የሜዳ ኮድ አማካይነት ሰዎች ስልክ ቁጥሩን አሊያም የሜዳ መለያ ስሙን (username) ማወቅ ሳይጠበቅባቸው የሜዳ ኮዱን ስካን አድርገው ቻት ማድረግ እና ገንዘብ መላላክ ይችላሉ።

መሠረታዊ

በዓለም አቀፍ ደረጃ የኪውአር ኮድ በስምምነት ስታንዳርድ የወጣላቸውን በርካታ የኪው.አር ኮድ አይነቶች ሜዳ ላይ ይሠራሉ። ለምሳሌ የግለሰብ መረጃ (MECARD)፣ ስልክ ቁጥር (TEL)፣ አጭር መልእክት (SMS)፣ ሁነት ወይም ዝግጅት(EVENT)፣ ቦታ (GEO LOCATION)፣ ዋይፋይ (Wi-Fi) በቀላሉ በሜዳ ስካን በማድረግ ለሁሉም የኪው.አር ኮድ አግባብነት ያለው ድርጊት መፈፀም ሜዳ ያስችላል። ለምሳሌ የዋይፋይ ኪው.አር ኮድ በሜዳ ስካን ቢያደጉ ሜዳ በቀጥታ ከዋይፋዩ ጋር ስልክዎን ያገናኘዋል። እንዲሁም የግለሰብ መረጃ ስካን ቢያደጉ አዲስ አድራሻ መመዝገቢያ ከስልዎ ላይ ያመጣልዎታል።

አየር ሰዓት

ሜዳ ላይ የአየር ሰዓት መሙላት ቀላል ነው። ተጠቃሚዎች ሜዳ ላይ የገዙትን አየር ሰዓት በቀላሉ ለመሙላት ኪው አር ኮድን መጠቀም ይቻላቸዋል።

 

እንግዲህ በጊዜ ሒደት የሜዳ ኮድ እየሰፋ፣ እየሰፋ በሀገራችን የኪው አር ኮድ ተጠቃሚነትን ለመጨመር እንዲሁም ነገሮችን በቀላሉ እና በፈጣን ሁኔታ የመፈፀም አቅምን ለመጨመር  የራሱን አሻራ እንደሚያሳርፍ አንጠራጠርም።

360_admin

Share
Published by
360_admin

Recent Posts

ICT Expo Ethiopia 2019

ICT Expo Ethiopia 2019 opened on 6 June 2019 At the Millennium Hall. Deputy Prime…

2 years ago

ውይይት በ‹‹ሜዳ ቻት››

በሻሂዳ ሁሴን አቶ ብሩክ ኃይሉ የስሪ ሲክስቲ ግራውንድ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ ስሪ ሲክስቲ ከተቋቋመ…

2 years ago

Meda Chat team on Fana TV

https://www.youtube.com/watch?v=rtgJbWfJOCI&feature=share

2 years ago

Meda Chat on Kana TV #Shikela

ከቃና ቴሌቪዥን ጋር ስለሜዳ ቻት ያደረግነውን ቆይታ ይመልከቱ #ሜዳቻት #የሜዳክፍያ #ሽቀላ https://www.youtube.com/watch?v=Qoq9ZfGaPZU&amp

2 years ago

AAES Horse Jumping Competition

[gallery type="rectangular" ids="73190,73189,73192,73191"]

2 years ago

ከ አዲስ ቲቪ ሳይ ቴክ ፕሮግራም ጋር ያደረገነው ቆይታ

https://www.youtube.com/watch?v=CTk-gl31MTQ Source: Addis TV

2 years ago